የልጆች አስተዳደግ በዚህ ዘመን
ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ፣ የትውልድ መሸጋገርያ ድልድይ፣ የአንድ ሀገር ቀጣይነት ህልውና መሰረት ናቸው። ከጊዜ ወደጊዜ እየተከሰተ ያለው ዓለም አቀፍ ለውጥ በየትኛውም ጉዳይ ላይ ራሳችንን ከዘመኑ ጋር እንድናራምድ እና የሚጠቅመንን እንድንለይ ግድ ይለናል። ዘመኑን ያማከሉ ሥነ-ዘዴዎችን ማወቅ እና የዘመኑ ልጆችን ፍላጎት ማጥናት ተገቢነት ይኖረዋል። ልጆች ከወላጆቻቸው በደም የሚወርሷቸው ባህርያት ቢኖሩም አብዛኛውን መገለጫቸውን የሚያገኙት ከቤተሰብ፣ ከማኅበረሰብ እና ከትምህርት ቤት እንደሆነ ቀደምት ጥናቶች ያመለክታሉ። በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉትን ወላጆች በልጆች አስተዳደግ ዙሪያ ያሉባቸውን ችግሮች በመገንዘብ እና ጥናትን መሰረት ያደረገ "የልጆች አስተዳደግ በዘህ ዘመን፥ ተግዳሮቶቹ እና መፍትሔዎቹ" በሚል ርዕስ ይህ መጸሐፍ ተዘጋጅቷል።
መጽሐፉ በስምንት ምዕራፎች ተከፍሎ የሚከተሉትን ነጥቦች ይዟል:-
- የልጅን ትርጉም ከቤተሰብ፣ ከማኅበረሰብ እና ከሀገር አንጻር
- የልጆች ዕድገት፣ የባህርይ ለውጣቸው እና ፍላጎታቸው በስነ-ልቦና ባለሞያዎችን ቀመር እና የወላጆች ሚና
- ወላጆች ለልጆቻቸው የሚያቀርቧቸውን መጫወቻዎች፣ የቴክኖሎጂ እና የቴሌቪዥን አጠቃቀም፣ የልጆች የመስክ እይታ፣ የገንዘብ አያያዝ፣ የትምህርት አጠናን ዘዴን እና የልጆች የስራ ባህል ምን መምሰል አለበት
- በአሁኑ ወቅት የተለመዱትን ወላጅ መር (አምባገነን)፣ አሳታፊ፣ መረን እና ቁብ የለሽ የተባሉትን የልጆች አስተዳደግ ጠንካራ እና ደካማ ጎን
- በልጆች የሚፈጸሙ ጥፋቶችን እና የእርምት እርምጃዎችን ከባለሞያዎች አስተያየት ጋር
- ውጤታማ እና ጤናማ ልጆችን ለማፍራት ባለድራሻ አካላት እነማናቸው?
- ከኢትዮጵያ ውጪ ያሉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በልጅ አስተዳደግ ያሉባቸው ችግሮች፣ መንሰኤዎቻቸው እና መፍትሔዎች
- በልጅ አስተዳደግ ወላጅ የለውን በራስ መተማመን እና ለልጅ የሚያስፈልጉትን መሰረታዊ ነግሮች እያደርገ እንደሆን ራሱን መመዘኛ ያስቀምጣል።
ይህ መጽሐፍ ከተለመደው የመጸሐፍ አቀራረብ ስልት በሦስት ነገሮች ይለያል። በመጀመሪያ በልጆች አስተዳደግ ዙሪያ የተጻፉ መጽሕፍት እና ጥናቶች ከተዳሰሱ በኃላ መሰረታዊ ንድፈ ኃሳቦች በማስቀመጥ፤ በመጠይቅ፣ በቃለ መጠይቅ እና በጋራ ውይይት የተሰበሰቡ መረጃዎችን በመተንተን እና በተሞክሮ (Case study) መልክ አስቀምጧል፤ ትኩረት ለሚያስፈልጋቸው ርዕሶች ሃሳቦችን በግጥም ስንኝ በመግለጽ እና አንባብያን መጽሐፉን ከአነበቡ በኋላ ወላጅ እራሱን የሚመዝንበት አሃዛዊ መለኪያም ያቀርባል።
መጽሐፉን ለመግዛት ይህን ይጫኑ