የአማርኛ መማሪያ ዲቪዲ ለጀርመንኛ ተናጋሪዎች

£11.99

ይህ የአማርኛ ማስተማሪያ ዲቪዲ ውበት ያለው፣ መስህብነት ባለው መልኩ እና በስዕል የተደገፈ የትምህርት መርጃ መሳርያ ነው። አዘገጃጀቱ ለሁሉም የእድሜ ክልል ደረጃ እና ልምድ ላሉ ህጻናትና ሌሎች አማርኛን ለመማር ለሚፈልጉ ሁሉ እንዲመች ተደርጎ የተዘጋጀ ነው። ህጻናቶቹ ይህን ታላቅ ቋንቋ ከጥንታዊና በባህል ከበለጸገችው ከኢትዮጵያ ታሪክ ጋራ እንዲማሩ እድሉን ይከፍትላቸዋል። የዲቪዲ ዝግጅቱ የተማሪዎችን ትኩረት ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የሚያስችል አቅም አለው። በውስጡም ከ ፬፻ በላይ የሚሆኑ የአማርኛ ቃላቶችን ከጀርመንኛ ትርጓሜያቸው ጋር አጣምሮ የያዘ ነው። ዲቪዲውን በኮምፒውተር ውስጥ ወይንም በቴሌቪዥን መስኮት(በዲቪዲ ማጫወቻ) ተጠቅመው መመልከት ይቻላል።

በዲቪዲው ውስጥ የሚከተሉትን ነገሮች ይማራሉ

  • ፴፫ የአማርኛ ፊደላትን ከ ፬፻ በላይ የአማርኛ ቃላቶች ጋር
  • ልዩ የሆነውን የኢትዮጵያን ታሪክና ባህል
  • በልዩ ህብረቀለማት ስለሚያሸበርቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በዓላት
  • ስለ ኢትዮጵያ ቁጥሮች
  • ስለባህላዊ የኢትዮጵያ ህጻናት ጨዋታዎች
Price: £11.99